STEM ፈጣሪ ወጣቶች

ቀጣዩን ትውልድ በኤስ.ቲ.ኤም ስራ ፈጠራ እና ችግር ፈቺነት በመላ ኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ የወጣቶችን በአማካሪ እና ሙያዊ መመሪያ/ ድጋፍ እንዲሁም በ ተግባር ተኮር የ ኤስ.ቲ.ኤም እውቀትን ተግባር ላይ እንዲውሉ ማስቻል

የፕሮግራሙ አጠቃላይ እይታ

ምልከታ

ኤስ.ቲ.ኤም ኢኖቬተር ወጣቶች አማካሪ እና ሙያዊ መመሪያ/ ድጋፍ ወጣቱ በ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ምህንድስና እና ሂሳብ ዘርፍ ፍላጎት ኖሮት እንዲሰራና ከጥያቄ መጠየቅ ወደ ፈጠራ እንቅስቃሴ እንዲሸጋገር ያስችለዋል። ደረጃውን በጠበቀ ምክር እና ሙያዊ መመሪያ/ ድጋፍ እንዲሁም ተግባራዊ ተሞክሮ, ተሳታፊዎች አስፈላጊውን ክህሎትና አስተሳሰብ ተቀርጾባቸው ዲጅታልና ሳይንሳዊ መሪነት ይይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የኤስ.ቲ.ኤም ኢኖቬተር ወጣቶች ፕሮግራም የተዘጋጀው ወጣቱን በተሞክሮ ትምሀርት ፣ በፈጠራ ውድድሮች እንዲሁም በቀጥታ አማካሪ እና ሙያዊ መመሪያ/ ድጋፍ ከ ቴክኖሎጂ፣ እና ምርምር ባለሙያዎች እንዲያገኙ ነው።

    የፕሮግራም አካሄድ

    ምዕራፍ 1፡መፈለጊያ (ከሳምንት 1-8 )

    የኤስ.ቲ.ኤም አማራጮችን መገንዘብ፣ ጠንካራ ጎኖችን መፈለግ እንዲሁም ከባለሙያዎች ጋር መገናኘት

    ምእራፍ 2፡ አዳዲስ አስተሳሰቦችን ማፍለቅ (ከሳምንት 9-15 )

    ተግባር ተኮር ፕሮጀክቶችን በቡድን ስራዎች እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳቦችን ከባለሙያዎች ጋር መስራት

    ምእራፍ 3፡ ተግባር ላይ ማዋል (ከሳምንት 16-24 )

    የፐሮቶታይፕ ሞዴል መስራት፣ የመፍተሄ ሃሳብ ያላቸውን ፕሮጀክቶችን መስራት፣ ለስራ ና ለንግድ ዕድሎች ዝግጁ መሆን

    የፕሮግራሙ ጥቅሞች

    Discover practical experience and professional exposure in high-demand STEM fields.

    የፈጠራ አስተሳሰብ መያዝ

    በጥልቅ የማሰብን፣ የፈጠራ ክህሎትን እና ፕሮጀክት የመቅረጽ ክህሎትን ማዳበር

    ቴክኒካል እድገት

    በተግባሩ ዓለም ላይ ያሉ የኤስ.ቲ.ኤም መተግበሪያዎችን በፕሮጀክት በመታገዝ መማር

    የባለሙያነት ዝግጁነት

    ፖርቲፎልዮ ማዘጋጀት፣ በኤስ.ቲ.ኤም እና ኢኖቬሽን ላይ ካሉ ባለ ሙያዎች ጋር መገናኘት

    የብቃት መስፈርት

    አጠቃላይ መስፈርቶች

    የዕድሜ ወሰን (ከ17 -27)

    በኤስ.ቲ.ኤም እና ኢኖቬሽን ዙርያ ፍላጎት ያላቸው

    በቴክኖሎጂ መሰረታዊ እውቀት ያላቸው ወይም ፍላጎት ያላቸው

    ለ24 ሳምንቶች ከ 5-8 ሰአታት በሳምንት መስጠት የሚችሉ

    የመተግበሪያ ሂደት

    1

    ማመልከቻ ያስገቡ

    በክፍት ጊዜ ውስጥ ኦላይን የማመልከቻ ቅጹን ይሙሉ

    2

    ደረጃ 2-አመልካቾችን መገምገም

    ቡድናችን ብቁ እና ከፕሮግራሙ ግቦች ጋር መጣጣምን ለማረጋገጥ አመልካቾችን ይገመግማል

    3

    ምርጫ

    እስከ ሃምሌ 15 ድረስ የእርስዎን ተቀባይነት ያገኛሉ

    ጉዞዎን ለመጀመር ዝግጁ ነዎት?

    ወደ ፊትዎ የመጀመሪያውን እርምጃ ይውሰዱ። በምክር ፕሮግራማችን አማካኝነት ህይወታቸውን የቀየሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይቀላቀሉ።

    አሁኑኑ ያመልክቱ