በኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ ወጣት ሴቶችን በራስ መተማመናቸውን በማሳደግ፣ ችግር ፈቺ መሪዎችን በ ሙያዊ ድጋፍ ማምጣት፣ ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች እና አማካሪዎች ጋር ወጣቶችን ማገናኘት፣ ወጣት ሴቶችን የ ማብቃት ስራን ያካትታል።
እቴጌ ጣይቱ ብጡልን ምሳሌ በማድረግ ፤ የወጣት ሴቶችን የአመራር ክህሎትን በራስ መተማመን እና አስፈላጊ ክህሎቶችን እገዛ በማሳደግ በወደፊት ህይወታቸው እና ማህበረሰብ ላይ ለውጥ እንዲያመጡ ይሰራል። ጣይቱ የወጣት ሴት አመራሮች በውስጡ ምክር እና ሙያዊ መመሪያ/ ድጋፍ፣ የ አመራርነት ስልጠና እንዲሁም ወጣት ኢትዮጵያውያንን በማገናኘት ጠንካራ ጎናቸውን እንዲያዳበሩ እና ለወደፊት ስንቅ የሚሆናቸውን ጉልበት እንዲይዙ ይረዳል።
በራስ መተማመንን መገንባት፣ ቅድሚያ የሚሰጡ ነገሮችን መለየት፣ ወጣት ሴቶችን እንዲነቃቁ ማድረግ
በወርክሾፖች ላይ በመገኘት የመግባቦት፣ የድርድር ውይይት ስምምነቶችን ማዳበር እንዲሁም የሃቀኛ መሪነት ልምዶችን በቡድን ሆኖ በሚሰጡ ፕሮጀክቶች ላይ ማዳበር
በግል ወይም ማህበረሰብ ላይ ለውጥ የሚያመጡ ፕሮጀክቶች ላይ የቀሰሙትን እውቀት ተግባራዊ ማድረግ
ወጣት ሴቶችን በራስ መተማመን እና ሙያዊ ልህቀት በአማካሪ እና ሙያዊ መመሪያ/ ድጋፍ ማብቃት
በራስ ማመን እና በየትኛውም ሁኔታ ላይ የመምራትን ብቃት ማኮትኮት
የተለያዪ ማህበረሰብ ተኮር ለውጥ አምጪ ጉዳዮችን መቅረጽ መቻልና ተግባር ላይ ማዋል
ወጣት ሴት መሆን (ዕድሜ ከ18-28)
የምስራቅ አፍሪካዊ ዜግነት መያዝ
መሪነት፣ ራስን ማብቃት እና ማህበረሰብ ላይ ለውጥ የማምጣት ፍላጎት ያላት
ለ24 ሳምንቶች ከ 5-8 ሰአታት በሳምንት መስጠት የምትችል
በክፍት ጊዜ ውስጥ ኦላይን የማመልከቻ ቅጹን ይሙሉ
ቡድናችን ብቁ እና ከፕሮግራሙ ግቦች ጋር መጣጣምን ለማረጋገጥ አመልካቾችን ይገመግማል
እስከ ሃምሌ 15 ድረስ የእርስዎን ተቀባይነት ያገኛሉ
ወደ ፊትዎ የመጀመሪያውን እርምጃ ይውሰዱ። በምክር ፕሮግራማችን አማካኝነት ህይወታቸውን የቀየሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይቀላቀሉ።
አሁኑኑ ያመልክቱ